ይህ ወቅት መጪውን ታሪካችንን በደማቁ የምንፅፍበት አዲስ ምዕራፍ ነው – ኢንጂነር ታከለ ኡማ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ትልቅ ሀገር ፣ ታላቅ ሕዝብን ማገልገል ክብርም መታደልም ነው፤ ወቅቱም መጪውን ታሪካችንን በደማቁ የምንፅፍበት አዲስ ምዕራፍ ነው ሲሉ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገለጹ።
በዛሬው ዕለት የማዕድን ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ኢንጂነር ታከለ ኡማ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ ትልቅ ሀገር ፣ ታላቅ ሕዝብን ማገልገል ክብርም መታደልም በመሆኑ ስለተጣለብኝ እምነትና ኃላፊነት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድን ከልብ አመሰግናለሁ ብለዋል።
ተፈጥሮ በራሷ ዑደትና ጥበብ የቸረችንን ፀጋ ተጠቅመን ለትውልድ የምትሆን ሀገር እንገነባለን ፣ ገንብተን ለትውልድ እናሻግራለን ሲሉ ነው የገለጹት።
የተቀበልኩት ሀላፊነት አደራም ጭምር ነው ያሉት ኢንጂነር ታከለ፥ መጪው ጊዜ የበለጠ የምንሰራበት ፣ የበለጠ የምናሳካበት ብሩህ ጊዜ መሆኑን ጠቁመዋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!