የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ፋውንዴሽን ተመሠረተ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምን ራዕይና ስራዎች የሚያስቀጥል ፋውንዴሽን ተመሠረተ።
የኘሮፌሰሩ ዕረፍት አንደኛ አመት መታሰቢያና የፋውንዴሽኑን ምስረታ አስመልክቶ አዘጋጅ ኮሚቴው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥትዋል።
በዚህ ወቅት የፋውንዴሽኑ ሊቀመንበር ዶክተር በድሉ ዋቅጅራ እንዳሉት ፕሮፌሰር መስፍን ሙሉ ህይወታቸውን ለአገር የሰጡ ናቸው።
ፕሮፌሰሩ ኢትዮጵያ ከድህነት የተላቀቀች፣ሰላም፣ሰብአዊ መብትና የሕግ የበላይነት የሰፈነባት ለማድረግ ሲሰሩ እንደነበር መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በስማቸው የተመሰረተው ፋውንዴሽን በማኅበረሰብ ሳይንስና በሠብዓዊ መብት ላይ ምርምር ለሚያካሂዱ ዜጎች ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረው ፋውንዴሽኑ ዓመታዊ አውደ ጥናት በማዘጋጀት የጥናትና ምርምር ስራዎች እንዲካሄዱ ያደርጋልም ተብሏል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!