የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ለከፍተኛ የመንግስት ሃላፊነት ቦታዎች ሹመቶች ሰጡ

By Meseret Awoke

October 07, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለከፍተኛ የመንግስት ሃላፊነት ቦታዎች ሹመቶች ሠጡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት አቶ ተፈሪ ፍቅሬን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ሃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አድርገው በድጋሚ ሾመዋል፡፡

ለአራት ከፍተኛ የሃላፊነት መደቦችም በሚኒስቴር ማእረግ የሚከተሉትን ሹመቶች ሰጥተዋል፡-

1. አቶ አደም ፋራህ – በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ

2. አቶ ተስፋዬ ቤልጅጌ – በሚኒስትር ማዕረግ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ

3. ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ – በሚኒስትር ማዕረግ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የህዳሴግድብ ዋና ተደራዳሪና አማካሪ

4. ዶክተር ለገሰ ቱሉ – በሚኒስትር ማዕረግ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ

በተጨማሪም፡-

– ዶክተር ምህረት ደበበ – የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚዳንት፤

– አቶ ፍሰሃ ይታገሱ – የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ፤

– እንዲሁም አቶ አብዱራህማን ሩቤ – የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው መሾማቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!