የሀገር ውስጥ ዜና

ደቡብ ኮሪያ ለኢትዮጵያ ዘመናዊ የንብ ቀፎ መቆጣጠሪያ ድጋፍ አደረገች

By Meseret Awoke

October 07, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኮሪያ መንግስት ዘመናዊ የንብ ቀፎ መቆጣጠሪያ ለግብርና ሚኒስቴር ድጋፍ አደረገ፡፡

ማሽኑ በንቦች ላይ ምንም አደጋ ሳያስከትል የደረሰውን ማር ብቻ ከቀፎው ለማውጣት የሚረዳ ነው ተብሏል፡፡

የማሽኑ ክብደት ቀላል ስለሆነ ከቦታ ቦታ ለማንቀሳቀስ እና ለአጠቃቀም ምቹ በመሆኑ ማንኛውም ንብ አናቢ በቀላሉ መጠቀም እንደሚያስችል ተጠቅሷል፡፡

ለሙከራ የመጡት ማሽኖች ለሆለታ ምርምር ማዕከል፣ ያዩ እና ሸካ የእናት ንብ ማራቢያና ማሰልጠኛ ማዕከላት ተልኮ በዘርፉ በተሰማሩ ባለሙያዎች በሙከራ ከተረጋገጠ በኋላ በቀጣይ ግለሰቦች፣ ባለሀብቶች እና ማህበራት ገዝተው እንዲጠቀሙ ይደረጋል ነዉ የተባለዉ፡፡

በርክክብ ስነ ስርዓቱ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ እና የደቡብ ኮሪያ ተወካዮች በተገኙበት ርክክብ መካሄዱን ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!