በአፋር ክልል በአሸባሪው ህወሃት ለተፈናቀሉ ወገኖች 3 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል በአሸባሪው ህወሃት ለተፈናቀሉ ወገኖች የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ የኦሮሚያና የሐረሪ ክልሎች የሴት አደረጃጀቶች 3 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት ሰብዓዊ ድጋፍ አደረጉ።
የድጋፉ አስተባባሪ በቀድሞ ስሙ የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ሙና አህመድ እንደተናገሩት አሸባሪው ቡድን በአማራና አፋር ክልሎች በንጹሃን ላይ በየፈጸመው ግፍና የጅምላ ጭፍጨፋ ታሪክ ይቅር የማይለው ነው።
የጦርነቱ ግንባር ቀደም ተጎጂዎች ሴቶችና ህጻናቶች በመሆናቸዉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተለያዩ ሰብአዊ ድጋፎች ሲያደርግ መቆየቱንም ትላንት ድጋፉን ለክልሉ ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ባስረከቡበት ወቅት ተናግረዋል።
ዜጎቹ ወደ ቀደመ ህይወታቸው እስከሚመለሱ ድረስም ሰብአዊ ደጋፎችን ተጠናከረዉ እንደሚቀጥሉ አስረድተዋል።
በዚህ መሰረትም የሴቶች አደረጃጀቶችን በማስተባበር ከ3 ነጥብ 5ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ምግብና ምግብ ነክ ድጋፍ መደረጉን አብራርተዋል።
የኦሮሚያ ክልል ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ምክትል ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ሠሚራ ፋሪስ እንደተናገሩት አሸባሪው ቡድን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጠላትነቱን የሚያስመሰክር የሃገር ክህደት ፈጽሟል።
የአፋር ክልል ሴቶችና ህጻናትጉዳይ ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ኤሻ ያሲን እንደተናገሩት በክልሉ አሸባሪው ህወሃት በፈጸመው ጥቃት ከ200 ሺህ የሚበልጡ ዜጎችን ከመኖሪያ ቤታቸዉ ከማፈናቀሉም ባለፈ በደረሰባቸው ቦታዎች ሁሉ ከፍተኛ ዘረፋና የመሰረተ ልማት ውድመት አድርሷል።
የደረሰውን ከፍተኛ ዉድመት ለማስተካከልም ሆነ ተፈናቃዮችን ወደ መደበኛ ህይወታቸው ለመመለስ በክልሉ መንግስት አቅም ብቻ የማይቻል በመሆኑ የሁሉም ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!