የሀገር ውስጥ ዜና

የማዕረግ ተሿሚዎች ለተጨማሪ ግዳጅና ሀላፊነት ራሳችሁን ማዘጋጀት ይገባል – ብ/ጄ ዶ/ር ሀይሉ እንዳሻው

By Alemayehu Geremew

October 07, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የጦር ሀይሎች ኮምፕሬሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተሻለ የስራ አፈፃፀምና የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ አመራሮችና አባላት የማዕረግ ዕድገት ሰጠ፡፡

በመርሃ ግብሩ የተገኙት የሆስፒታሉ አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል ዶክተር ኃይሉ እንዳሻው ተሿሚዎች ለበለጠ ኃላፊነትና ለተጨማሪ ግዳጆች ራሳቸውን ማዘጋጀት እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል።

ማዕረግ ባደገ ቁጥር ለህዝባችን ያለን ታማኝነት፣ ተቆርቋሪነትና ታታሪነት በመጨመር የበለጠ ሀገራችንን ለማገልገል ራሳችንን ማዘጋጀት ይገባል ብለዋል፡፡

በዚሁ መሠረትም ተሿሚዎች በሁሉም መስክ ራሳችሁን ማዘጋጀት ይኖርባችኋል ነው ያሉት፡፡

ተሿሚዎችም የማዕረግ ዕድገቱ እንዳስደሰታቸውና ህዝብና መንግስት የሰጣቸውን ሀላፊነትም በበለጠ ሁኔታ ለመወጣት ዝግጁ ነን ማለታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡