የሀገር ውስጥ ዜና

በንፁሃን ዜጎቸ ላይ ጥቃት ለመፈፅም በህቡዕ  ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የሸኔ ታጣቂዎች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

By Meseret Demissu

October 07, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ጉጂ ዞን በንፁሃን ዜጎቸ ላይ ጥቃት ለመፈፅም በህቡዕ  ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የሸኔ ታጣቂዎች ላይ  እርምጃ መወሰዱን ለመረጃው ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን አረጋገጡ

ከሽብርተኛው ህወሓት ጋር ጥምረት በመፍጠር በኦሮሚያ ክልል አንድ አንድ አካባቢዎች በንፁሃን ዜጎች ላይ

ጥቃት ለመፈፅም በህቡእ እየተንቀሳቀሰ ያለው ሽብርተኛው የሸኔ ቡድን ሰሞኑን በምስራቅ ጉጂ ዞን በጎሮ

ዶላ ወርዳ አዳዲ ቀበሌ እና ልዩ ቦታው ሙጋዮ በተባሉ አካባቢዎች የጥቃት ሙከራ ለማድረግ ታጣቂዎቹን

አስርጎ ለማስገባት መሞከሩ ተገልጿል።

ሆኖም የቡድኑን እንቅስቃሴ በሚስጥር ሲከታተሉ  በነበሩ የመንግስት ፀጥታ አካላት በወሰዱትእርምጃ ሴራው መክሸፉንና የጥፋት ተልዕኮ  ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የቡድኑ አባላትም መደምሰሳቸውን ለመረጃው ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን አረጋግጠዋል።

የቡድኑን የሽብር ጥቃት ከማክሸፍ በተጨማሪም የፀጥታ አካላት በአሸባሪው የሸኔ ቡድን ላይ በወሰዱት

እርምጃ በርካታ የቡድኑ ታጣቂዎች ሙትና ቁስለኛ ሲሆኑ ፥በርካቶች መማረካቸውም ተጠቁሟል፡፡

ቡድኑ እየተወሰደበት ያለውን እርምጃ ተከትሎ ሟቾቹ እንዳይታወቁበት እሬሳ ይዞ ሲሸሽ እንደነበር

የጠቁሙት ምንጮቻችን ፥ በቡድኑ አባላት ላይ በተወሰደው እርምጃ ከቆሰሉት መካከልም ታጣቂ ሀይሉን

ሲመሩ ነበሩ የቡድኑ ከፍተኛ አመራሮች እንደሚገኙበትም አረጋግጠዋል።

ሽብርተኛውን የሸኔን ቡድን እግር በእግር በመከታተል ሴራውን የማክሸፍና የመደምሰሱ ሂደት ተጠንክሮ መቀጠሉንም ምንጮቻችን  ከስፍራው አረጋግጠዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!