የሀገር ውስጥ ዜና

የመንግስት አካላት ከህዝብ የተጣለባቸዉን አደራ በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባ የህግ ባለሙያዎች ጠቆሙ

By Meseret Awoke

October 07, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) አስፈጻሚ አካላት ከህዝብ የተጣለባቸዉን አደራ በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸዉ የህግ ባለሙያዎች ተናገሩ ፡፡

በሚዛን ቴፒ ዪኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍልና የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ አቶ መሃመድ ሰኢድ÷ መንግስት የህግ ተጠያቂነትን በአግባቡ ገቢራዊ ማድረግ እንደሚገባው ጠቁመዋል ፡፡

ከአቶ መሃመድ ሰኢድ ሃሳብ ጋር የሚስማሙት እና የህግ ባለሙያና ጠበቃ የሆኑት አቶ ፋሲል ስለሺ በበኩላቸው ÷ አስፈጻሚ አካላቱን ወደ ሌብነት የሚወስዱ ልል የመንግስት አሰራሮች ማሻሻል አለባቸው ብለዋል፡፡

የህግ ባለሙያዎቹ አክለውም ከዚህ ቀደም ጥርስ የሌለዉ አንበሳ ሆኖ የቆየዉ የህዝብ እንደራሴው አካል ጠንካራ እና እዉነተኛ ስራዎችን ተግባራዊ ማድረግ እንዳለበትም ሃሳባቸዉን አካፍለዋል ፡፡

ተሿሚዎች ለጋራ ሃገር በሚደረገዉ ጥረት ውስጥ ለህሊናቸዉ ተጠያቂ በመሆን ከህዝብና ከመንግስት የተጣለባቸውን አደራ በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባም አስረድተዋል ፡፡

በአወል አበራ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!