እስራኤል በሶሪያ ደማስቆ አቅራቢያ በኢራን የሚደገፉ ሀይሎች ላይ የአየር ጥቃት ፈፀመች
አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) እስራኤል በሶሪያ ደማስቆ አካባቢ በሚንቀሳቀሰው እና በኢራን በሚደገፈው ሀይል ላይ እርምጃ መውሰዷ ተገለፀ።
ሳና የዜና አገልግሎት እንዳስነበበው ከእስራኤል የተተኮሱ በርካታ ሚሳኤሎችን መመከት ቢቻልም፤ ስምንት ሰዎች ላይ ግን ጉዳት ደርሷል ብሏል።
በጥቃቱ ጉዳት ከደረሰባቸው ሰዎች በተጨማሪም በኢራን እንደሚደገፉ የሚነገርላቸው 12 ታጣቂዎች መሞታቸውንም ከስፍራው የወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
እስራኤል ስለ ጥቃቱ አስተያየት ከመስጠት ብትቆጠብም፤ በያዝነው ዓመት ገን የኢራን ጦር የእጅ አዙር እንቅስቃሴን ለማስቆም በሞቶዎች የሚቆጠሩ ሚሳኤሎችን ማስወንጨፏን አረጋግጣለች።
እራን እና አጋሮቿ፤ የሊባኖሱን ሄዝቦላህ ጨምሮ በሶሪያ እየተካሄደ ባለው የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ለፕሬዚዳንት በሽር አላዛር ታማኝ የሆኑ ሀይሎችን እንደሚደግፉ ነው የሚነገረው።
ምንጭ፦ ቢቢሲ