የሀገር ውስጥ ዜና

በአቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራው ልዑክና የማክሮ ኢኮኖሚ ቡድን በአዳሚ ቱሉ ኩታ ገጠም የበቆሎ ማሳ ጎበኘ

By Alemayehu Geremew

October 08, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራው ልዑክና የማክሮ ኢኮኖሚ ቡድን በአዳሚ ቱሉ ወረዳ የሚገኘውን ኩታ ገጠም የበቆሎ ማሳ መጎብኘቱ ተገለጸ፡፡

በወረዳው በእርሻ ሥራ ላይ ከተሰማሩ 157 አርሶ አደሮች ናቸው፡፡

በአርሶ አደሮቹ የለማ 240 ሄክታር ኩታገጠም መሬት የበቆሎ ማሳ በልዑካን ቡድኑ ተጎብኝቷል፡፡

የክልሉ ግብርናና ተፈጥሮ ኃብት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ጌቱ ገመቹ ÷ በወረዳው የተመረተው የበቆሎ ምርት በኦሮሚያ ደረጃ በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡

በክልሉ 1 ነጥብ 6 ሚሊየን ሄክታር መሬት ላይ እየለማ እንደሚገኝ ኃላፊው የገለፁት ኃላፊው በኩታ ገጠም 90 በመቶ ያህሉን የሚሸፍነው የበቆሎ ምርት ነው ተብሏል፡፡ ከዚህም መሬት ላይ 65 ሚሊየን ኩንታል የበቆሎ ምርት ለማግኘት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አርሶ አደሮቹ በበኩላቸው ተጠቃሚውንና አርሶ አደሩን የሚያገናኝ የገበያ ትስስር አለመፈጠሩ ፈተና እንደሆነባቸው ገልጸዋል፡፡

ኃላፊውም በበኩላቸው ችግሩን ለመፍታት ቢሯቸው ምርቱ የሚከማችበት እና ለገበያ የሚያቀርብበትን ሁኔታ እንደሚያመቻች ገልፀዋል፡፡

ጀሚላ ጀማል እና አዲሱ ሙሉነህ