የሀገር ውስጥ ዜና

ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ በኢትዮጵያ ከቻይና አምባሳደር ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

October 08, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ በኢትዮጵያ  ከቻይና  አምባሳደር ዛሆ ዛይሁዋንና ከቻይና የኢኮኖሚ እና የንግድ ጉዳዮች ሚኒስተር ኮንስላር ሩ ያንግ ዪ ሃንግ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይቱ በሁለቱን ሀገራት የረጅም ጊዜ የኢንቨስትመንት ግንኙነት በፕሮሞሽን፣ በአፍተር ኬር ፕሮግራም እንዲሁም በተለያዩ የልምድ ልውውጦች ማጠንከር፣ ከቻይና ባለሃብቶች ጋር ተደጋጋሚ የትስስር መድረኮችን በመፍጠር ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡