እየተሰሩ ባሉ ስራዎች ላይ ተጨማሪ እያከልን የተሰጠንን ኃላፊነት ለመወጣት እንሰራለን – ረዳት ፕሮፌሰር በለጠ ሞላ
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 29 ፣2014 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አዲስ የተሾሙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ረዳት ፕሮፌሰር በለጠ ሞላ ከቀድሞው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር አብረሃም በላይ የስራ ርክክብ አድርገዋል።
የመከላከያ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ዶክተር አብረሃም በላይ ፥ሀገራችንን ወደ ፊት ለማሻገር በቀጣይም በተለያዩ ጉዳዮች በጋራ መስራታችንን እንቀጥላለን ብለዋል።
አዲስ ለተሾሙት ሚኒስትርም መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ረዳት ፕሮፌሰር በለጠ ሞላ፥ እስከ ዛሬ የተሰሩ ስራዎች ላይ ተጨማሪ እያከልን ሀገራችንንና ህዝባችንን ለማገልገል እንሰራለን ብለዋል።
ተቋሙ በቅብብሎሽ እየተመራ እዚህ ደረጃ የደረሰ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፥ ከተቋሙ ሰራተኞች ጋር ውጤታማ ስራ ለመስራት የሚጠበቅብንን ሁሉ እናደርጋለን ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+3
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like
Comment
Share