Fana: At a Speed of Life!

የአንድነት ፓርክን ከግማሽ ሚሊየን ባላይ ዜጎች ጎብኝተውታል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሃሳብ አመንጪነትና የቅርብ ክትትል ተጠናቆ ለጎብኝዎች አገልግሎት መስጠት የጀመረው አንድነት ፓርክ ዛሬ 2ኛ ዓመቱን አከበረ፡፡
ፓርኩ በሃገር ገጽታ ግንባታ፣ የቱሪዝም እንቅስቃሴ ላይ የጎብኝዎችን ቁጥር ከማሳደግና ከስራ እድል ፈጠራ አኳያ በሁለቱ ዓመታት ውስጥ ትልቅ ሚና መጫወቱን የአንድነት ፓርክ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ታምራት ሃይሌ አስረድተዋል፡፡
በሁለቱ አመታት ውስጥ 590 ሺህ ጎብኝዎች የጎበኙት ሲሆን÷ ከእነዚህ ውስጥ 25 ሺህ የሚሆኑት የውጭ ዜጎች ናቸው ተብሏል፡፡
ከጎብኝዎቹ መካከልም 487 ሺህ የሚሆኑት በክፍያ የገቡ መሆናቸውን የጠቆሙት ሥራ አስኪጁ÷ ከ100 ሺህ የሚልቁት ደግሞ ያለክፍያ በነፃ ጉብኝት መግባታቸውን ገልጸዋል።
ከስራ ዕድል ፈጠራ አንጻርም በመቶዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠሩንም ተናግረዋል።
የአንድነት ፓርክ በኮቪድ 19 ምክንያት ለ6 ወራት ተዘግቶ እንደነበር የሚታወስ ነው
በቆንጂት ዘውዴ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.