የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ከአፍሪካ ተጠቃሚነት ኮርፖሬሽን አባላት ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

October 10, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በአሜሪካ በሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች ከተቋቋመው የአፍሪካ ተጠቃሚነት ኮርፖሬሽን አባላት እና ከፌደራል ህብረት ሥራ ኤጀንሲ የሥራ አመራሮች ጋር ተወያዩ፡፡

በዚህ ወቅት የአፍሪካ ተጠቃሚነት ኮርፖሬሽን ከህብረት ሥራ ማህበራትም ሆነ ከአነስተኛ ገበሬዎች ጋር በመተባበር ምርቶቻቸውን ወደ ውጭ በሚልኩበት መንገድ ላይ ያያዘው ዕቅድ ላይ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡