ስፓርት

የኢትዮጵያ ውሃ ዋና ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ሻምፒዮና ለመሳተፍ ወደ ጋና አቀና

By Feven Bishaw

October 10, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ውሃ ዋና ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ውሃ ዋና ሻምፒዮና ለመሳተፍ ወደ ጋና አክራ አቅንቷል።

ጋና በምታዘጋጀው የአፍሪካ የውሃ ዋና ሻምፒዮና ላይ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመካፈል የኢትዮጵያ ውሃ ዋና ብሔራዊ ቡድን ስምንት የልዑካን አባላትን በመያዝ ወደ አክራ ማቅናቱን ከኢትዮጵያ ውሃ ስፖርቶች ፌደሬሽን ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡