Fana: At a Speed of Life!

ለቻይና ተሃድሶ ዳግም ውህደት ግድ ነው – ቺ ጂንፒንግ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የቻይናው ፕሬዚዳንት ቺ ጂንፒንግ÷ በ1911 በፈነዳው የሀገሪቷ አብዮት 110ኛ ዓመት የመታሰቢያ ክብረ በዓል ላይ፣ ለቻይና ተሃድሶ ዳግም ውህደት የግድ አስፈላጊ መሆኑን ተናገሩ፡፡

ቺ ጂንፒንግ ÷ ቤጂንግ በሚገኘው ታላቁ የስብሰባ አዳራሽ፣ የአብዮቱን 110ኛ ዓመት ባከበሩነት የመታሰቢያ ስብሰባ ላይ እንደተናገሩት ካለፈው ትምህርት ወስደን የቻይናን ዳግም ውህደት እናሳካለን ዳግምም እንታደሳለን ብለዋል፡፡

ቺ÷ በቀጣይ ከታይዋን ጋር በመነጋገር ለሠላማዊ እና ብሔራዊ ውህደት እንደሚሰሩም ነው የጠቆሙት÷ ፕሬዚዳንቱ ቀድሞም ቢሆን ታይዋንን ከቻይና መነጠል ታሪክን የተቃረነ እና አደገኛ አዝማሚያ ነበር ሲሉ በስብሰባው ተደምጠዋል፡፡

ቺ÷ ታይዋን ለዚህ የበቃችው በእኛ ድክመትና ሀገራችን ውስጥ በተፈጠረው አለመረጋጋት ነው ብለው÷ በቀጣይ ጉዳዩ መፍትሄ እንደሚበጅለት ብሎም የቻይና ተሃድሶ እውን እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ÷ የታይዋን ጥያቄ የቻይና የውስጥ ጉዳይ በመሆኑ የማንም ጣልቃ ገብነት እንደማያስፈልግ እና ውህደቱ እውን እንደሚሆን አስምረውበታል፡፡

ይህ ዘመን ተሻጋሪ ውህደት ቻይናዊያን ሲጓጉለት የነበረ የጋራ ፍላጎት ነውም ብለዋል በንግግራቸው፡፡

የዛሬ 110 ዓመት በዶክተር ሱን ያት ሴን የተመራው የ1911 አብዮት የቻይናውያንን ዳግም ውህደት ወሳኝ እና ረጅም አድካሚ ምዕራፍ መጀመሪያ ያመላከተ እንደሆነም ሲ ጂቲ ኤን አመላክቷል፡፡

በዓለማየሁ ገረመው

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.