የሀገር ውስጥ ዜና

ተለዋጭ የዓባይ ወንዝ ድልድይ ግንባታ 41 ነጥብ 1 በመቶ ደረሰ

By Feven Bishaw

October 11, 2021

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 1፣2014 (ኤፍ ቢሲ)እየተገነባ የሚገኘውን ተለዋጭ የዓባይ ወንዝ ድልድይ ግንባታ የስራ ሂደት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለና የሥራ ኀላፊዎች ጎብኝተዋል፡፡

በባሕር ዳር ከተማ እየተገነባ የሚገኘው ይህ ተለዋጭ የዓባይ ድልድይ በቻይና ኮንስትራክሽን ኮምዩኒኬሽን ካምፓኒ ነው ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘው፡፡