Fana: At a Speed of Life!

በብዝሃ ሕይወት ጥበቃና ክብካቤ ላይ ያተኮረ ጉባዔ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና አነሳሽነት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተጠራው 15ኛው የሥነ ህይወት ስምምነት ጉባዔ በደቡብ ምዕራብ ቻይና ዩናን ግዛት ኩንሚንግ ከተማ በይፋ ተጀመረ።
የሥነ ምህዳር ሥልጣኔ፥ ለሁሉም የወደፊት ሕይወት የጋራ ግንባታ በሚል መሪ ቃል የተካሄደውና በብዝሃ ህይወት ላይ ያተኮረው ይህ ጉባኤ ÷በብዝሀ ሕይወት ጥበቃና ክብካቤ ላይ ቻይና መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል ስትራቴጂያዊ እቅድና የድርጊት መርሃ ግብር እንደምትቀይስ የቻይናው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሃን ዜንግ በጉባዔዉ መክፈቻ ላይ ተናግረዋል።
ይህ የሥነ ህይወት ስምምነት ጉባኤ 15ኛ ስብሰባ በዓይነቱ በተባበሩት መንግስታት የተጠራ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ ጉባኤ እንደሆነ ሲጂቲኤን ዘግቧል።
ሀገሪቱ በብዝሀ ሕይወት ጥበቃ ላይ ግንዛቤ ፣ ትምህርትን እና እውቀትን በማጠናከር ህብረተሰቡ በብዝሀ ሕይወት ጥበቃ ላይ በንቃት እንዲሳተፍ ትመክራለች ተብሏል፡፡
የቻይናው ፕሬዚደንት ዢ ጂንፒንግ ነገ በስብሰባዉ ላይ በቪዲዮ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የጉባዔዉ ተሳታፊዎች÷የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም እና በተፈጥሮ ላይ የተመሠረተ ሥነ ምህዳራዊ ጥበቃን ጨምሮ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዉይይት ያደርጋሉ ነዉ የተባለዉ፡፡
እ.ኤ.አ. በ 1993 በሥራ ላይ በዋለው የሥነ ህይወት ስምምነት አካል ከሆኑት አገሮች መካከል ቻይና የመጀመሪያዋና የሃሳቡ አፍላቄ መሆኗ ተወስቷል።
የጉባኤው ተሳታፊዎች የዓለም ብዝሃ ሕይወት ማዕቀፍ ልማትና ኢንቨስትመንትን ማሳደግ ላይ ትኩረት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በሻምበል ምህረት
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.