ኡጋንዳ በኮሮና ቫይረስ ስጋት 100 ሰዎችን በለይቶ ማቆያ ስፍራ እንዲቆዩ አደረገች
አዲስ አበባ ፣ ጥር 29 ፣ 2012 (ኤፍቢሲ) ኡጋንዳ በኮሮና ቫይረስ ስጋት 100 ሰዎችን በለይቶ ማቆያ ስፍራ እንዲቆዩ አደረገች።
የኡጋንዳ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ጃኔ ሩት የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል በሚል ከ100 በላይ ሰዎች በለይቶ ማቆያ ስፍራ እንዲቆዩ መደረጉን ተናግረዋል።
በለይቶ ማቆያ ስፍራው የሚቆዩት ሰዎችም ለ14 ቀናት ክትትል ይደረግላቸዋል ብለዋል።
ሰዎቹ ከቻይና ወደ ኡጋንዳ የመጡ ሲሆን፥ ከእነዚህ ውስጥ 44ቱ ቻይናውያን ዜጎች ናቸው ተብሏል።
የተወሰኑት በቤታቸው በህክምና ባለሙያዎች ክትትል የሚደረግላቸው ሲሆን፥ ቀሪዎቹ ደግሞ በተዘጋጁ የለይቶ ማቆያ ማዕከላት ክትትል ይደረግላቸዋል።
የሃገሪቱ ባለስልጣናት በቻይና የሚኖሩ ኡጋንዳውያንን የመመለስ እቅድ እንደሌላቸው አስታውቀዋል።
የቫይረሱ መነሻ በሆነችው የቻይናዋ ውሃን ከተማ 70 ኡጋንዳውያን ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ይገኛል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision