Fana: At a Speed of Life!

የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት ለ150 ዓይነ-ሥዉራን ዘመናዊ አጋዥ መሳሪያ አበረከተ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ለ150 ዓይነ-ሥዉራን ዘመናዊ አጋዥ መሳሪያ አበረከተ፡፡

መሳሪያዉ ከእስራኤል ሀገር በመጡ ባለሙያች አማካኝነት ከቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር ለ150 ዓይነ-ሥዉራን ከሥልጠና ጋር መሰጠቱ ተገልጿል፡፡

ኦርካም ሚየየ የተሰኘዉ መሳሪያ መጽሃፍትን ጋዜጣ ወይም መጽሄት የመንገድ ምልክቶችን ሞባይል እንዲሁም ስክሪን ላይ የተጻፉ ነገሮችን ያነባል፡፡

በሱፐር ማርኬት ዉስጥ ተጠቃሚዉ በቀላሉ እንዲገበያይ ይረዳዋል፤እንዲሁም በርካታ ሌሎች አገልግሎቶችን ይሰጣል፡፡

ጽህፈት ቤቱ በዚህ አመት የሚጠናቀቀዉን የኤፍ.ቢ.ኤም አዳሪ የዓይነ-ሥዉራን ትምህርት ቤት በ400 ሚሊየን ብር እየገነባም ይገኛል፡፡

ትምህርት ቤቱ 300 ዓይነ ሥዉራንን የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል የተባለ ሲሆን ÷ከተለያዩ ለጋሽ አገራት ከሚያገኘዉ ድጋፍ ለዓይነ-ሥዉራንና ሌሎች አካል ጉዳተኞች የሚያደርግዉን ድጋፍ እደሚቀጥል ተገልጿል፡፡

በፈትያ አብደላ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.