Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የሴቶች ዓሣ አቀነባባሪዎች እና ነጋዴዎች ማኅበር ተመሰረተ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የሴቶች ዓሣ አቀነባባሪዎች እና ነጋዴዎች ማኅበር ተመሰረተ።

ምስረታውን ተከትሎም ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሴቶች ዓሣ አቀነባባሪዎችና ነጋዴዎች ኔትዎርክ አባል መሆኗ ይፋ ተደርጓል።

የማኅበሩ መመስረት በአገር፣ በአህጉር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የገበያ ትስስርን በማጠናከር ከዘርፉ ተጠቃሚ መሆን የሚቻልበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እንደሚረዳ ተገልጿል።

በግብርና ሚኒስቴር የዓሣ ሃብት ልማት ዳይሬክተር አቶ ሁሴን አበጋዝ ማኅበሩ በአገር አቀፍ ደረጀ እንዲቋቋም የተፈለገው በዘርፉ በተሰማሩ ባለሙያዎች መካከል የእውቀት ሽግግር እንዲኖርና የገበያ ትስስሩን ለማጠናከር እንደሆነ ተናግረዋል።

ከአፍሪካ አገራት ጋር የሚያስተሳስር በመሆኑ ሴቶች የአቅም ግንባታ እንዲያገኙ፣ ምርቶቻቸውን በጥራት እንዲያቀርቡና በጎረቤት አገራት መሸጥ የሚያስችላቸውን ዕድል እንደሚፈጥርም ገልጸዋል።

የአፍሪካ የዓሣ አቀነባባሪዎችና ነጋዴዎች ማኅበር ምክትል ፕሬዚደንት ሱዛን ጄሪ በበኩላቸው፤ በምርምር ላይ ላሉ ሴቶች፣ አገልግሎት ሰጪዎችና በሚኒስቴር ደረጃ ካሉ ሴቶች ጋር መስራት የሚያስችላቸው በመሆኑ ራሳቸውን ለማብቃትና ለማሳደግ ይረዳቸዋል ብለዋል።

የአፍሪካ ሴቶች ዓሣ አቀናባሪዎችና ነጋዴዎች ኔትዎርክ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2017 የተቋቋመ ሲሆን፥ ከ30 በላይ አባል አገራት አሉት።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.