Fana: At a Speed of Life!

የቡድን 20 አባል ሃገራት ለአፍጋኒስታን እርዳታ ለማድረግ ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 3፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የቡደን 20 አባል ሃገራት የአፍጋኒስታንን ሰብዓዊ ቀውስ ለማስወገድ እርዳታ ለማድረግ መስማማታቸዉ ተገለፀ።
የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪዮ ድራጊ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት የአፍጋኒስታን ሰብአዊ አደጋን ለማስወገድ በጋራ ለመስራት ይኖርብናል ብለዋል።
የአዉሮፓ ሕብረት በከፈተዉ ይህ ጉባኤ 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ሰምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን ፥ድጋፉም በአፍጋኒስታን አስቸኳይ የሰባዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸዉ ዜጎች ይዉላል ነዉ የተባለዉ፡፡
በቡድን 20 አባል ሀገራቱ ስብሰባ ላይ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ፣ የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ እና የአውሮፓ መሪዎች ተሳትፈዋል፡፡
የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ እና የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ደግሞ ተወካዮቻቸዉን መላካቸዉ ነዉ የተገለፀዉ፡፡
ምንጭ፡- አልጀዚራ
በሚኪያስ አየለ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.