Fana: At a Speed of Life!

የቻይና የመስከረም ወር ወጪ ንግድ ማደጉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 3፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ቻይና በመስከረም ወር በአሜሪካ ዶላር የፈጸመችው የወጪ ንግድ ግብይት በ28 ነጥብ 1 በመቶ ማደጉ ተገለጸ፡፡

ገቢ ንግዷ ደግሞ ካለፈው ወር አንፃር በ17 ነጥብ 6 በመቶ መቀነሱ ተመላክቷል፡፡

ቻይና በመስከረም ወር የ305 ነጥብ 74 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ወጪ ንግድ እና የ238 ነጥብ 98 ቢሊየን ዶላር ገቢ ንግድ መፈጸሟን የሀገሪቷ የንግድ ልውውጥ መረጃዎች አመላክተዋል፡፡

ሊ ኩዌን የተባለ የሀገሪቷ ጉምሩክ ባለሥልጣን ቃል አቀባይ÷ ቻይና በወጪና ገቢ ንግዷ አወንታዊና አሉታዊ ተጽዕኖዎች እንዳስተናገደች ጠቁሞ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአቅርቦት ፍላጎት ማደጉ ለቻይና ወጪ ንግድ ማደግ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል ብሏል፡፡

የሸቀጦች ዋጋ መጨመር ደግሞ ከውጪ የምናስገባቸው ምርቶች ላይ የዋጋ ማሻቀብ አስከትሎብናል ብሏል – ሊ ኩዌን፡፡

ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ፍላጎት ጋር የሚጣጣም አቅርቦት ለማድረስ ደግሞ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኃይል አቅርቦት ዋጋ አለመረጋጋቱ እና ሀገሪቷ እየተከተለች ካለችው ታዳሽ ኃይል የመጠቀም አማራጭ አንጻር ፋብሪካዎቿ የኃይል አቅርቦት እጥረት እያጋጠማቸው እንደሆነ ነው የጠቆሙት፡፡

አሁን ላይ የኃይል አቅርቦት እጥረት እና ከኮቪድ 19 ቫይረስ ወረርሽኝ ማገርሸት ጋር ተያይዞ የዓለም ኢኮኖሚ በተፈለገው ልክ ባለማገገሙ እንዲሁም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተወሳሰበ በመምጣቱ በንግዱ ላይ ቀጣይ ስጋት ሊሆን እንደሚችልም ሊ ኩዌን ጠቁመዋል፡፡

ምንጭ÷ሲጂቲ ኤን

በዓለማየሁ ገረመው

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.