በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርስቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ አባላት እዉቅና ሰጠ
አዲስ አበባ፣ጥቅምት 3፣2014 (ኤፍ . ቢ .ሲ) በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርስቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ፣ በስራ አፈፃፀማቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ አባላትና ሲቪል ሰራተኞች ዕውቅና የመስጠትና የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ ባለ ሌላ ማዕረግተኞች የማልበስ ስነ-ስርዓት አከናውኗል።
የመከላከያ ስፔሻላይዝድ ኮምፕረሲቭ ሆስፒታል አዛዥ ብ/ጄ ተገኝ ለታ ፥ ኮሌጁ ብቁ ወታደር የህክምና ሙያተኞችን በማፍራት ለሰራዊታችን የግዳጅ አፈፃፀም ስኬታማነት የማይተካ ሚና እየተጫወተ ይገኛል ብለዋል፡፡
የዕለቱ ተሿሚዎችና ዕውቅና የተሰጣችሁ የሰራዊት አባላትም ለተጨማሪ ኃላፊነት በመዘጋጀት ሃገራችሁ ከእናንተ የምትጠብቀውን ሁሉ ማድረግ ይጠበቅባችኋል ብለዋል።
የጤና ሳይንስ ኮሌጅ አዛዥ ኮ/ል ደምሌ ቢረሳው በበኩላቸው ፥ የኮሌጁ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ውጤታማ ተግባራትን ከማከናወናቸውም ባለፈ ፣ የኮቪድ -19 ወረርሽኝ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ ግምት ውስጥ በማስገባት ትርጉም ያለው ጫና ሳያሳድር መቆጣጠር እንዲቻል ተሿሚዎችና ዕውቅና የተሰጣቸው አባላት ከፍተኛ አስተዋፅዖ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
የማዕረግ ዕድገት ካገኙና ዕውቅና ከተሰጣቸው የሰራዊት አባላት መካከል አንዳንዶች በሰጡት አስተያየት ፣ ዕውቅናና የማዕረግ ዕድገቱ የበለጠ የስራ ሞራልና ተነሳሽነት የሚፈጥር ፣ የሚሰጠንን ማንኛውም ግዳጅ በብቃት ለመወጣት የሚያስችል መሆኑን መናገራቸዉን ከመከላከያ ሰራዊት የፌስቡክ ገፅ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+2
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like
Comment
Share