Fana: At a Speed of Life!

የዓየር ንብረት ለውጥ 85 በመቶ በሚሆነው የዓለም ክፍል ተጽዕኖ አሳድሯል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 85 በመቶ የሚሆነው የዓለማችን ክፍል የዓየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ተጋላጭ መሆኑን ሣይንሣዊ ጥናቶች አመላከቱ፡፡
በጀርመን በርሊን ከሚገኙት ክላይሜት አናላይቲክስ እና ሜርካተር የጥናት ኢኒስቲትዩት የተውጣጡ አጥኚዎች ከ 1951 እስከ 2018 የተካሄዱ 100 ሺህ ያህል የጥናት ውጤቶችን በቴክኖሎጂ በመታገዝ ተመልክተዋል፡፡
በምልከታቸውም÷ በዓየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በምድር ስርዓት ላይ በሁሉም ክፍለ ዓለማት ተፅዕኖ መድረሱን ነው የገለጹት፡፡
እንደ ጥናት ቡድን መሪው ማክስ ካላጋን ገለጻ÷ የአየር ንብረት ለውጥ ለአእዋፋት መሰደድ እና ለደን ውድመት ብሎም ለሰው ልጅ ሕይወት መቀጠፍ መንስኤ መሆኑንለ አብነት ጠቅሷል፡፡
ምንጭ፡- ሲ ጂ ቲ ኤን
በዓለማየሁ ገረመው
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.