39ኛው የአፍሪካ ህብረት የአስፈፃሚ ም/ቤት መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ይጀመራል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)ከኮሮና ወረረሽኝ መከሰት ወዲህ በአካል በአዲስ አበባ የሚካሄደው 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የአስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛው ስብሰባ ከጥቂት ሰዓት በኋላ ይጀመራል።
ትኩረት በሚያሻቸው በአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ይካሂዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ስብሰባው ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት እንደሚካሄድ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!