በአማራ ክልል በ421 ሚሊየን ብር አዳዲስ የመስኖ ፕሮጀክቶች ሊገነቡ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአማራ ክልል በ421 ሚሊየን ብር 200 አዳዲስ የመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ ሊጀመር መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
በክልሉ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ከተያዙ 118 ነባር የመስኖ ፕሮጀክቶች መካከል 89ኙ እስከ ቀጣዩ መጋቢት 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ይጠናቀቃሉ ተብሏል።
በመጋቢት ወር ይጠናቀቃሉ ለተባሉ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያም ከ142 ሚሊየን ብር በላይ በጀት መመደቡም ነው የተለጸው።
ፕሮጀክቶቹ ተጠናቀው ወደ ሥራ ሲገቡ 219 ሺህ 274 ሄክታር መሬት ያለማሉ ተብሎም ይጠበቃል።
በግንባታ ሂደት ላይ ከሚገኙት ፕሮጀክቶች በተጨማሪ 421 ሚሊየን ብር በጀት የተመደበላቸው 200 ዘመናዊ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ እንደሚጀመርም በቢሮው የመስኖ መሐንዲስ አቶ ኃይሉ እንግዳየሁ ተናግረዋል።
ነባሮቹን እና አዳዲስ የሚጀመሩትን ፕሮጀክቶች በታቀደላቸው ጊዜ በማጠናቀቅ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሠራ ቢሮው ማስታወቁን ከአማራ መገናኛ ብዙሃን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በክልሉ ካሉ የመስኖ ፕሮጀክቶች መካከል 29 የሚሆኑት ተጠናቀው አግልግሎት መስጠት ጀምረዋል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision