የሀገር ውስጥ ዜና

ቤኒን በአዲስ አበባ ኤምባሲ ለመክፈት ተዘጋጅታለች

By Meseret Demissu

October 14, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ማጠናከር የምትፈልገው ቤኒን በአዲስ አበባ ኤምባሲ ለመክፈት መዘጋጀቷ ተገለጸ።

በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ከሚገኘው 39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ ጎን ለጎን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከቤኒን አቻቸው ኦሬሊየን አግቤኒቺ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

ውይይቱን የተከታተሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ኢትዮጵያ እና ቤኒን የሁለትዮሽ ትብብራቸውን በሚያጠናክሩባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ገልጸዋል።

“ቤኒን በአዲስ አበባ ኢምባሲዋን ለመክፈት መዘጋጀቷንና አምባሳደር እንደሾመችም በውይይቱ ላይ ተነስቷል” ብለዋል።

ቤኒን ከኢትዮጵያ ጋር በሁሉም መስኮች ለመተባበር ዝግጁ መሆኗንም አግቤኒቺ ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!