Fana: At a Speed of Life!

በኮንጎ ኢቦላ ተከሠተ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ኪቩ ግዛት፣ በኢቦላ ቫይረስ የተያዘ ሁለተኛው ሰው በጤና ባለሙያዎች ተመዘገበ፡፡

በኢቦላ ቫይረስ እንደተያዘ የታወቀው የመጀመሪያው ታማሚ ወጣት ሲሆን÷ በሰሜን ኪቩ ግዛት በሚገኘው ቤኒ ጤና ጣቢያ ሕክምና ሲከታተል ቆይቶ ከሣምንት በፊት ሕይወቱ ማለፉ አይዘነጋም፡፡

የቤኒ ጤና ዞን የሕክምና ኃላፊ የሆነችው ሚቼል ቶሳሊሳና ÷ በሀገሪቷ 2ኛ ሆኖ የተመዘገበው የኢቦላ ቫይረስ ተጠቂ የ42 ዓመት ሴት መሆናቸውን ገልጻለች፡፡

በትናንትናው ዕለት የሀገሪቷ የጤና ባለሥልጣናት ከዓለም ጤና ድርጅት ጋር በመተባበር በሰሜን ኪቩ ግዛት የኢቦላ ክትባት ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ያስታወቁ ሲሆን÷ 1ሺህ የመከላከያ ክትባት(ዶዝ) እና ሌሎች የሕክምና ቁሶች ወደ ሰሜን ኪቩ ጎማ ከተማ መላካቸውም ነው የተመላከተው፡፡

200ው የቫይረሱ መከላከያ ክትባት ደግሞ የቫይረሱ ምልክት ወደተስተዋለበት ቤኒ መላኩ ነው የተጠቆመው፡፡

ካለፈው የኢቦላ ወረርሽኝ ወዲህ በሀገሪቷ በኢቦላ ቫይረስ የተያዙ ዜጎች ቁጥር 12 መሆኑን እና የሥድስቱ ሕይወት ማለፉን መረጃዎች ያሳያሉ ሲል የዘገበው ሲጂቲ ኤን ነው፡፡

በዓለማየሁ ገረመው

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.