የሀገር ውስጥ ዜና

የወምበራ ወረዳ ማህበረሰብ ለሰራዊቱ ድጋፍ አደረገ

By Feven Bishaw

October 15, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመተከል ዞን የወምበራ ወረዳ ማህበረሰብ በግንባር ለሚገኙ የሰራዊት አባላት ድጋፍ አደረጉ፡፡

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙሉጌታ አዲሱ እንደተናገሩት÷ የወረዳው ህዝብ ሰራዊቱን ለመደገፍ በ560 ሺህ ብር ወጪ 15 በሬ ፣ 13 ፍየል ፣ 4 በግ እንዲሁም 10 ኩንታል እህል አዘጋጅተው አስረክበዋል ::