የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት በሚፈጠሩ ችግሮች ሳይሸነፍ የነገ ብሩህ ተስፋዋን ዕውን የሚያደረግ አመራር ነው-ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

By Feven Bishaw

October 15, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት በየጊዜው በሚፈጠሩ ችግሮች ሳይሸነፍ የነገ ብሩህ ተስፋዋን ዕውን የሚያደረግ አመራረ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ ያሉት በአፍሪካ ልህቀት ማዕከል ሲሰጥ የነበረውን የከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ማጠናቀቂያ መድረክ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ነው።