የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ የዓለም አቀፍ የገጠር ሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ በአፍሪካ ሕብረት የተዘጋጀውን ጉባዔ ከፈቱ

By Feven Bishaw

October 15, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የዓለም አቀፍ የገጠር ሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ በአፍሪካ ሕብረት የተዘጋጀውን ጉባዔ በይፋ ከፈቱ ።

በጉባዔው ባደረጉት ንግግር ÷የገጠር ሴቶችን ዘመናዊ የግብርና ቴክኒኮችን ፣ የጤና መረጃዎን እና ሌሎች የህይወት ክህሎቶችን እንዲያገኙ በማድረግ ወደ 21 ኛው ክፍለዘመን ለማሸጋገር አገራት ወሳኝ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል።