የሀገር ውስጥ ዜና

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራ ልዑክ በኦሮሚያ ክልል የግብርና ስራዎችን እየጎበኘ ነው

By Meseret Awoke

October 16, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6 ፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ በኦሮሚያ ክልል የግብርና ስራዎችን እየጎበኘ ነው።

የፌዴራል እና የክልል መንግስታት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና አዲስ የተሾሙ ሚኒስትሮች በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን አደኣ ወረዳ ተገኝተው በኩታ ገጠም የለሙ እህሎች፣ አትክልት እና ፍራፍሬዎችን እየጎበኙ ነው።

የኩታ ገጠም የእርሻ ስራ አርሶ አደሮችን ይበልጥ እንዲተሳሰሩ አድርጓቸዋል ሲሉ የገለጹት የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ÷ አርሶ አደሮች እንዲያለሙ ከማድረግ ጎን ለጎን በጋራ እንዲያቅዱ፣ ተመሳሳይ ቴክኖሎጂ እንዲጠቀሙ እና ምርት እንዲያመርቱ በመደረጉ ይበልጥ እንዲቀራረቡ እድል ፈጥሯል ነው ያሉት።

ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም ለአርሶ አደሮች የሚሰጠው ትኩረት ይበልጥ ይጠናከራል ብለዋል።

ጉብኝቱ ዛሬና ነገ እንደሚቀጥል ይጠበቃል።

ከሰሞኑ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተመራ ልዑክ በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች የተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር የግብርና ስራዎችን መጎብኘቱ ይታወቃል።

በደበላ ታደሰ

ተጨማሪ ፎቶ:- ከኦቢኤን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!