Fana: At a Speed of Life!

በቀጣይ ሣምንት የፖሊዮ ክትባት ሊሠጥ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀጣይ ሣምንት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ሕፃናት የፖሊዮ ክትባት ሊሰጥ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡
የክልሉ ጤና ቢሮ የሕዝብ ግንኙነትና ጤና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ዋጮ ዋቡልቾ እንደተናገሩት÷ በክልሉ ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ሕፃናት ከጥቅምት 12 እስከ 15/2014 ዓ.ም የፖሊዮ ክትባት ይሰጣል፡፡
ለክትባቱ መሳካት የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ዘርፉ የበኩሉን ሚና እንዲወጣም ጠይቀዋል፡፡
የክልሉ መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ በየነ በበኩላቸው÷ በቀጣይ ሣምንት የሚሰጠውን የፖሊዮ ክትባት ለማሳካት የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ሥራ ከወዲሁ መሥራት ይገባል ማለታቸው ከክልሉ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.