Fana: At a Speed of Life!

ከተማ አስተዳደሩ ለጎፋ የባህል ማዕከል የግንባታ ቦታ ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጎፋ የባህል ማዕከል የግንባታ ቦታ ሰጥቷል።

በመርሃ ግብሩ የጎፋ እድገትና ብልጽግና ማህበር የአዲስ አበባ ቅርንጫፍም በይፋ ተመስርቷል።

በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ በተከናወነው መርሃ ግብር የከተማ አስተዳደሩ ለጎፋ የባህል ማዕከል ግንባታ 5 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ አስረክቧል።

የጎፋና ኦይዳ ባህል ማዕከል በአዲስ አበባ ከተማ መቋቋም ከተማዋ የሁሉንም ኢትዮጽያዊያን ብሔር ብሔረሰቦች የባህል ሙዚየም እንድትሆን ማሳያ መሆኑን ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በመርሃግብሩ ገልጸዋል ።

በተጨማሪም የከተማዋን የቱሪዝም ዘርፍ በማሳደግ ገቢ ከማመንጨት ባለፈ የህዝቦችን አንድነት እና ፍቅር ከማጠናከር አንጻር ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል ።

የባህል ማዕከሉ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ የዞኑ ተወላጆች ተባብረው መስራት ይኖርባቸዋል ፤የከተማ አስተዳደሩም አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

የጎፋ ዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር ጌትነት በበኩላቸው ከወራት በፊት ለከተማ አስተዳደሩ የጎፋና ኦይዳ ህዝብ ባህልን ለማስተዋወቅ በቀረበው ጥያቄ መሠረት ፈጣን ምላሽ በመሰጠቱ ምስጋና ማቅረባቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.