Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን በምእራብ አርሲ ዞን ሴሮፍታ የግብርና ምርጥ ዘር ማባዣን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንንን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በምእራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ወረዳ ሴሮፍታ የግብርና ምርጥ ዘር ማባዣን ጎበኙ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፤ የሁለቱ ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎችንና ሚኒስትሮችን ያካተተ ልኡክ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የግብርና ምርት እየጎበኙ ይገኛሉ።

በሁለተኛ ቀን ጉብኝታቸው በምእራብ አርሲ ዞን የዶዶላ ወረዳ ሴሮፍታ የግብርና ምርት ምርጥ ዘር ማባዣን ጎብኝተዋል።

ኢትዮጵያን መለወጥ የሚቻለው ግብርና ሲዘምን በመሆኑ ይህ እውን እንዲሆን ሁሉም በየዘርፉ የሚጠበቅበትን ሃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባው የጉብኝቱ ተሳታፊዎች መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ በአምስት የተለያዩ አካባቢዎች በ32 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ምርጥ ዘር እያባዛ መሆኑ ታውቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.