Fana: At a Speed of Life!

የመውሊድ በአልን ለማክበር ወደ ጀማ ንጉስ መስጅድ የሚመጡ ምእመናንን ለመቀበል ዝግጅት ማጠናቀቁን የአልቡኮ ወረዳ አስተዳደር ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)1496 ኛውን የመውሊድ በአልን ለማክበር ወደ ጀማ ንጉስ መስጅድ የሚመጡ ምእመናንን ለመቀበል ዝግጅቱን ያጠናቀቀ መሆኑን በደቡብ ወሎ ዞን የአልቡኮ ወረዳ አስተዳደር ገለጸ።
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ መውሊድ በተከበረበት በጀማ ንጉስ መስጅድ በየአመቱ በአሉ በደማቅ ሀይማኖታዊ ስርአት ይከበራል።
ህዝበ ሙስሊሙ ወደ ቦታው ሲመጣ እንዳይቸገር የ12 ኪሎ ሜትር መንገድ ጠረጋ ስራ ፥ ጊዜያዊ የህክምና የፍትህ ተቋማት ማእከላት፣ የምግብና የሸቀጣሸቀጥ ሱቆችን ተደራጅተዋል።
የወረዳው ጤና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብዱ ሠይድ እንደገለጹት፥ ከንጽህና ጋር ተያያዥነት ያላቸው በሽታዎችን ለመከላከል የህክምና ቡድን ተደራጅቶ እየሠራ ነው ብለዋል።
ህብረተሠባችን ለሠላሙ ዋጋ በመስጠት በሀይማኖታዊ ስርዓት በአሉን ማክበር ይጠበቅበታል ያሉት የወረዳው መንግስት ኮሙኒኬሽን ሀላፊ አቶ አሊ አባተ ናቸው።
በክብረ በአሉ በርካታ ህዝበ ሙስሊም በቦታው ስለሚገኝ ለመረጃ ልውውጥ የሚያገለግል የሚኒ ሚዲያ አገልግሎት ተደራጅቷል ።
የወረዳው የጸጥታ አካላትም በዝግጁነት ህብረተሠቡን እያገለገሉ ይገኛሉ።
በአለባቸው አባተ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of outdoors and monument
70,126
People Reached
2,246
Engagements

-1.2x Average

Distribution Score
Boost Post
720
80 Comments
23 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.