ዓለምአቀፋዊ ዜና

የመዉሊድ በዓል በተለያዩ ሀገራት እየተከበረ ነዉ

By Meseret Awoke

October 18, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 496ኛው የመውሊድ በዓል በተለያዩ የዓለም ሃገራት እየተከበረ ይገኛል፡፡

በዓሉ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ የሚገኝ ሲሆን÷ የነብዩ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ) ውልደትን በማሰብ ተከብሮ ይውላል፡፡

ኢትዮጵያን ጨምሮ ግብጽ፣ ሱዳን፣ የመን እና ናይጀሪያ በዓሉን ከሚያከብሩት የአፍሪካ ሃገራት መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

በተጨማሪም በዓሉ በተለያዩ የአዉሮፓ እና እስያ ሃገራት በመከበር ላይ ነው፡፡

አዉስትራሊያ፣ ሩሲያ፣ ፓኪስታን፣ ባንግላዲሽ እና ፊሊፒንስ በዓሉን ከሚያከብሩ ሃገራት መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!