የሀገር ውስጥ ዜና

መውሊድ በደሴ ከተማ የሙስሊም እና የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች በተገኙበት በጋራ ተከበረ

By Alemayehu Geremew

October 18, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 496ኛው የነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዕ.ወ) የመውሊድ በዓል በደሴ ከተማ የክርስትና እና የሙስሊም ሃይማኖት ተከታዮች በተገኙበት በጋራ ተከብሯል፡፡

የደሴ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ሊቀመንበር ሼህ ሰይድ ኡመር እንኳን ለ1 ሺህ 496ኛው የነቢዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል።

አሚኮ እንደዘገበው÷ የመውሊድ በዓልን ለመከላከያ ሠራዊቱ ድጋፍ በማድረግ፣ ለተፈናቀሉ ወገኖች ማድ በማጋራት እና ሌሎች በጎ ተግባራትን በመከወን መከበሩን ገልጸዋል።

ለዚህም ሕዝበ ክርስቲያኑ እና ሙስሊሙ ድጋፍ ማድረጋቸውን አስረድተዋል። ማኅበረሰቡም የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት በዓሉን እንዲያሳልፍ ጠይቀዋል።