Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ፣ በእስራኤልና በአሜሪካ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችና ወዳጆች ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ፣ በእስራኤልና በአሜሪካ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችና ወዳጆች በሽብርተኛው ትህነግ ተፈናቅለው በደባርቅ ከተማ ለተጠለሉ ወገኖች የምግብና አልባሳት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ድጋፉን ካስረከቡት ተወካዮች መካከል አቶ ደረጀ ሽፈራው ለወገን ደራሽ ወገን ነው በሚል በአሜሪካ፣ በእስራኤል እና በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ከሚኖሩ የአማራ ተወላጆችና ወዳጆች በሰበሰቡት ከ1 ሚሊየን ብር በላይ የተገዛውን ምግብና አልባሳት ወደ ደባርቅ ማምጣታቸውን ገልጸዋል፡፡

ከተፈናቃይ ወገኖች ብዛትና ከችግሩ አሳሳቢነት አንፃር የተደረገው ድጋፍ በቂ አለመሆኑን ተናግረው ወደፊትም የተጠናከረ ድጋፍ ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡

ሌላኛው ተወካይ አቶ ጥጋብ አንበርብር አሸባሪው ትህነግ እንዲደመሰስና የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ አካባቢያቸው እንዲመለሱ ሁሉም ሊረባረብ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ድጋፉን የተረከበው የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽሕፈት ቤት በዞኑ ያለውን ችግር በመረዳት ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና ማቅረቡን አሚኮ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.