የዘማች ቤተሰብ ልጆችን ማስተማር የኛ ድርሻ ሊሆን ይገባል-የሰሜን ሸዋ ዞን ትምህርት መምሪያ
አዲስ አበባ፣ጥቅምት 9፤2014 (ኤፍ ቢሲ) የሰሜን ሸዋ ዞን ትምህርት መምሪያ ለ2014 የትምህርት ዘመን በዞኑ ከበጎ አድራጊ ባለ ድርሻ አካላት የተገኙትን የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፎች በየወረዳው ለሚገኙ የዘማች ቤተሰብ ልጆች እንዲከፋፈል ማድረጉን ገልጿል።
በዞኑ 2ሺህ 554 ሚልሻዎች 4ሺ972 ተማሪ ልጆች እንዳሏቸው የገለፁት የሰሜን ሸዋ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አይነኩሉ አበበ፤ የነዚህን ዘማች ቤተሰብ ተማሪዎች ቦርሳና ስቴሽነሪዎችን ከባለድርሻ አካላት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል።
በዚህ መልኩ ትምህርት ላይ መስራት ካልተቻለ ሀገር መቀጠል አትችልም ያሉት ኃላፊው፥ ዘማቾች የኛን ህይወት ለማቆየት ለዘመቻ ግንባር በመሄዳቸው እኛ የነሱን ልጆች የመማሪያ ግብዓት ማሟላት ይኖርብናል ፣ ስለዚህ የዘማች ቤተሰቦችን ልጆችን ማስተማር የኛ ድርሻ ሊሆን ይገባል ብለዋል።
እስካሁን ባለድርሻ አካላት ያሳዩት በጎ ተግባር የሚመሰገኑ ሲሆን፤ ሌሎችም በዚህ መልኩ ድጋፉን መቀጠል ይኖርባቸዋል ብለዋል።
በችግር ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎችን ለመደገፍ ደብረ ብርሃን ዩንቨርሲቲና በትምህርት መምሪያ በኩል ኮሚቴ ተዋቅሮ የተማሪ ግብዓቶች እየተሰበሰበ መሆኑንም ኃላፊው መጠቆማቸውን ከሰሜን ሸዋ ዞን ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን