Fana: At a Speed of Life!

የመነኩሴ ልብስ ለብሶ ሲያጭበረብር የነበረዉ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 9፤2014 (ኤፍ ቢሲ) በደብረ ብርሃን ከተማ የመነኩሴ ልብስ ለብሶ ሲያጭበረብር የነበረን አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የከተማው ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የፅህፈት ቤቱ ቤት ኃላፊ ኮማንደር ታዬ ሀብተጊዮርጊስ እንደተናገሩት÷መስከረም 27 ቀን 2014 ዓ.ም በከተማው ቀበሌ 2 አካባቢ ከጠዋቱ 4 ሰዓት የመነኩሴ ልብስ ለብሶ የተለያዩ ተልዕኮዎችን ለመፈፀም ሲንቀሳቀስ የነበረን አንድ ግለሰብ ነው በማህበረሰብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር በማዋል መረጃ ሲጣራ የቆየው፡፡

ተጠርጣሪው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ሲውል የመነኩሴ ልብስ ለብሶ ዳዊት ተክለአብ ወልደአማኑኤል የሚል የምንጃር ሸንኮራ አረርቲ ከተማ አስተዳደር የቀበሌ መታወቂያ በመያዝና በዚው በአረርቲ ከተማ የሚሊሻነት ስልጠና የወሰደበትን መታወቂያ ይዞ መገኘቱን ሃላፊዉ ተናግረዋል ፡፡

የያዘውን መረጃ ትክክለኛነት ለማረጋገጥም በተደረገው የማጣራት ስራ ተጠርጣሪው ግለሰብ የትውልድ ቦታው ጣርማ በር ወረዳ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ተጠርጣሪው የኃይማኖት ክህነት እንዳለውም ለማረጋገጥ ተሞክሮ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ቤተክህነትም ምንም አይነት የቅስና፣የክህነትም ሆነ የኃላፊንት ፈቃድ እንዳልተሰጠው የተረጋገጠ መሆኑን አስታውቀዋል ሃላፊዉ፡፡

አክለውም ይህ ግለሰብ ወደከተማው የገባው የጁንታውን ተልዕኮ ለማስፈፀም እንደሆነ ለማረጋገጥ መረጃዎች እየተጣሩ መሆኑን ጠቁመውል፡፡

ኮማንደር ታዬ በኃይማኖት ሽፋንም ሆነ በተለያየ መልኩ የትህነግን ተልዕኮ ይዘው በከተማው የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ሊኖሩ ስለሚችሉ ማህበረሰቡ የጀመረውን ጥበቃ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ገልጸዉ ጥርጣሬን የሚሳድር እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ግለሰቦች ሲኖሩም ለፖሊስ ጥቆማ መስጠት እንደሚገባ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳድር ኮሙዩንኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.