ዲፕሎማቶች የአገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ከምንግዜም በላይ መሥራት አለባቸው
አዲስ አበባ፣ጥቅምት 9፤2014 (ኤፍ ቢሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለዲፕሎማቶች፣ ለሠራተኞቹና ለተጠሪ ተቋማት ሠራተኞች በሁለት ዙር ያካሄደው ሥልጠና መጠናቀቁን አስመልክቶ የመዝጊያ መርኃ ግብር በወዳጅነት አደባባይ እያካሄደ ነው።
በመርኃ ግብሩ ላይ የታደሙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እንደተናገሩት፤ ሠልጣኞቹ በቆይታቸው ተልዕኳቸውን በብቃት ለመፈጸም የሚያስችላቸውን ክህሎት ጨብጠዋል።
ሰልጣኞቹ በቀጣይ ወደ ዲፕሎማሲው ሥራ ሲገቡ የአገራቸውን ገጽታ በመገንባትና የአገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም በላቀ ደረጃ ማስከበር እንደሚገባቸውም አሳስበዋል።
በተለይም አሁን በአገሪቱ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ የአገሪቱን እውነታ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የማሳወቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ሠልጣኞቹ በአስተሳሰብ ለውጥ፣ በተቋሙ የለውጥና የአደረጃጀት ሥራ፣ በዲጂታል ዲፕሎማሲና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ሥልጠና መውሰዳቸው ይታወሳል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!