Fana: At a Speed of Life!

መንግስት የውሸት የስራ ሪፖርቶችን ለማስቀረት ህብረተሰቡን የሚያሳትፉ ስልቶችን ተግባራዊ ማድረግ አለበት -ምሁራን

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 9፤2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት የውሸት የስራ ሪፖርቶችን ለማስቀረት ህብረተሰቡን የሚያሳትፉ ስልቶችን ተግባራዊ ማድረግ አለበት ሲሉ ምሁራን ተናገሩ።

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና ልማት ኢንስቲትዩት መምህር ዶክተር መሐመድ አሊና በጂማ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሃብት ክፍል ባልደረባ እጩ ዶክተር ብርሃኑ ጌታቸው እንዳሉት ÷ከዚህ ቀደም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በሚያቀርቡት ሪፖርት ብቻ በስልጣን እንዲቀጥሉ መደረጉ የውሸት ሪፖርት እንዲበራከት በር ከፍቷል።

የውሸት ሪፖርት እየተደጋገመ እርምት ሳይደረግበት መቀጠሉ ደግሞ መንግስት ከህዝብ ጋር ሆድ እና ጀርባ እንዲሆን በማድረግ ሲቪል ሰርቫንቱ በመንግስት የሚወጡ እቅዶች እንዲሳኩ ከማድረግ ይልቅ የስራ ሃላፊዎችን ስሜት መጠበቅ እንዲሆን አድርጓል ነው ያሉት ምሁራኑ።

አሁን ላይ የመንግስት የሞራል ደረጃ የሚያሳዩ ሁኔታዎች ማስተዋል ጀምረናል የሚሉት እጩ ዶክተር ብርሃኑ፤ መንግስት ከእውነት ጋር ለመጋፈጥ ያለውን ቁርጠኝነት እና በህዝብ መተማመን ለመፍጠር የሚያደርገው ጥረት ያመለክታል ነው ያሉት።

መንግስት የውሸት ሪፖርት ለማስቀረት ያለው ቁርጠኝነት በህዝቡ ካልተደገፈ ውጤት ለማምጣት አዳጋች በመሆኑ ህዝብን የሚያሳትፉ የተለያዩ ስልቶች ተነድፈው ተግባራዊ መደረግ ይገባቸዋል ብለዋል ዶክተር መሐመድ አሊ።

በዋናነትም ሪፖርት በመስረታዊነት የሚፈልቅባቸው ክልሎች በመሆናቸው የክልል መንግስታት የጠራ እና ትክክለኛ ሪፖርት እንዲያቀርቡ በማድረግ የውሸት ሪፖርት ምንጮችን ማድረቅ ይገባል ብለዋል ምሁራኑ፡፡

በበላይ ተስፋዬ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.