Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት ያለስምምነት ተበተነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት ያለስምምነት መበተኑ የተወሰኑ አገራት የራሳቸውን ጥቅም አስልተው ለሚያደርጉት ጫና ሌሎች አገራት ተባባሪ አለመሆናቸውን ያሳዬ ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለፁ።
የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ማዕቀብ ለመጣል ተሰብስቦ ያለስምምነት መጠናቀቁ ዋናው ምክንያት የተወሰኑ አገራት የራሳቸውን ጥቅም አስልተው ለሚያደርጉት ጫና አገራት ተባባሪ ሆነው መግፋት አለመፈለጋቸውን ያሳዩበት ነው ብለዋል።
አንዳንድ የአውሮፓ ህብረት አባል አገራትና ሌሎች በኢትዮጵያ ላይ የሚያራምዱት አቋም እውነታ ላይ ያልተመሰረተ በመሆኑ አጉል ልፋትመሆኑን ገልጸዋል።
አለመስማማታቸውም አንዳንድ አገራት ባላወቁት ነገር ውስጥ ተገፍተው ገብተው ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፍጠር መሞከር ተገቢ አለመሆኑን አመላካች ነውም ብለዋል ሲል ኢፕድ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.