Fana: At a Speed of Life!

የመከላከያ ሚኒስቴር ተቋማት ስኬታማ ተግባራትን እንዲያከናውኑ ስራና ሰራተኛን አገናኝተው እንዲሰሩ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ ከመስሪያ ቤቱ ተጠሪ ተቋማት አመራሮች ጋር ውይይት አደረጉ፡፡
ውይይቱም÷ ከመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ፣ ከፋይናንስ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ፣ ከመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር እንዲሁም ከመከላከያ ኮምኘሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አመራሮች ጋር ነው የተደረገው፡፡
ተቋማቱ ከተቋቋሙበት ዓላማ አንፃር ስኬታማ ተግባራትን እንዲያከናውኑ በተለይም ስራና ሰራተኛን አገናኝተው በተያዘው የበጀት አመት ውጤታማ የስራ አፈፃፀም እንዲኖራቸው አሳስበዋል።
የመከላከያ ኮምኘሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አዛዥ ብ/ጀ ተገኝ ለታ እንደገለጹት÷ የተጀመሩ መሠረተ ልማቶች ተገንብተውና የህክምና መሳሪያዎች ሙሉ በሙሉ ተገጥመውለት ሲጠናቀቅ ሆስፒታሉ በምስራቅ አፍሪካ ብቸኛው ሃይቴክ ሆስፒታል ይሆናል መባሉን ከመከላከያ ሚኒስቴር ማህበራዊ ገጽ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.