የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ዶ/ር ድረስ ሳህሉን በድጋሚ ተቀዳሚ ከንቲባ አድርጎ ሾመ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 4ኛ ዙር ምርጫ 10ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 22ኛ መደበኛ ጉባኤ ዶክተር ድረስ ሳህሉ በድጋሚ የባሕር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ ሆነው ተሹመዋል።
ዶክተር ድረስ ለከተማው ምክር ቤት ተቋማትን የሚመሩ አዳዲስ ተሿሚዎችን አቅርበው ማጽደቃቸውን አሚኮ ዘግቧል።
በዚህ መሠረት:-
1ኛ. ምክትል ከንቲባ – አቶ ባየ አለባቸው
2ኛ. በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ- ወይዘሮ ብርሃን ንጉሤ
3ኛ. የከተማ አገልግሎት ዋና ሥራ አስኪያጅ – አቶ ኃይለየሱስ ፀጋየ
4ኛ. የባሕር ዳር ከተማ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ – አቶ በትግሉ ተስፋሁን
5ኛ. የባሕር ዳር ከተማ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ – አቶ ኃይለማርያም እሸቴ
6ኛ. የባሕር ዳር ከተማ ሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች መምሪያ ኃላፊ – ወይዘሮ የሻረግ ፈንታሁን
7ኛ የባሕር ዳር ከተማ ሲቪል ሰርቪስ መምሪያ ኃላፊ – አቶ ጤናው ምህረቴ
8ኛ. የባሕር ዳር ከተማ ገቢዎች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ – አቶ ሙሉዓለም ተፈራ
9ኛ. የባሕር ዳር ከተማ ሰላምና ደኅንነት መምሪያ ኃላፊ – አቶ አደራ ጋሼን አድርጎ ሾሟል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!