Fana: At a Speed of Life!

የሀረሪ ክልል አዲስ መንግስት የፊታችን ዓርብ ይመሰረታል

የአዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል አዲስ መንግስት የፊታችን ዓርብ እንደሚመሰረት የክልሉ ምክር ቤት ድህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ነገኦ ተናግረዋል፡፡
 
ኃላፊው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ የሀረሪ ክልል አዲሱ ምክር ቤት የፊታችን ጥቅምት 12 ቀን 2014 ዓ.ም ይመሰረታል፡፡
 
በዚህም የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤና ምክትል አፈ ጉባኤ የሚሰየም መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
 
በተጨማሪም ምክር ቤቲ የሚቀርቡለትን የክልል ርዕሰ መስተዳድርና ምክትል ርዕሰ መስተዳድርን ጨምሮ የሌሎችን ስራ አስፈፃሚ አካላት ሹመት እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።
 
ላለፉት 6 ዓመታት በምክር ቤት አባልነት ሲያገልግሉ ለነበሩ የምክር ቤት አባላት በይፋ ሽኝት እንደሚደረግም ተመላክቷል፡፡
 
በተሾመ ኃይሉ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.