Fana: At a Speed of Life!

ወጣቶችና ሴቶች ሀገር ማዳን ዘመቻውን ለማሳካት የተጠናከረ ተሳትፎ እያደረጉ ነው- ማህበራት

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአገር ማዳን ዘመቻውን ለማሳካት አባሎቻቸው የተጠናከረ ተሳትፎ እያደረጉ መሆናቸውን የአማራ ክልል ወጣቶችና ሴቶች ማህበራት አስታወቁ።

የማህበራቱ ሊቀ መንበሮች እንደተናገሩት ÷የማህበራቱ አባላት አሸባሪው ህወሃት የከፈተውን ጦርነት ለመመከት ተሳትፎአቸውን እያጠናከሩ ነው።
የማህበሩ ሊቀ መንበር ወጣት አባይነህ ጌጡ አባላቱ አሸባሪው ቡድን ከፀጥታ መዋቅሩ ጎን በመሰለፍ የህይወት መስዋትነት በመክፈል ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በተጨማሪም ትጥቅና ስንቅ በአግባቡ እንዲቀርብ በማድረግና ሃብት በማሰባሰብ ደጀንነቱን እያሳየ መሆኑንና ለዘመቻው እያደረጉ ያለውን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል ።

“ኢትዮጵያ እንደ አገር፤ አማራ እንደ ሕዝብ የተረጋጋ ኑሮ የሚኖረው አሸባሪው ቡድን ወደ መጣበት እንዲመለስ በማድረግ ብቻ ሳይሆን ባለበት እንዲቀበር በማድረግ ነው” ብለዋል ።

አባላቱ ቡድኑ የሚነዛውን የሐሰት ፕሮፓጋንዳ በአግባቡ በመረዳት ህብረተሰቡን በማሳወቅና የማረጋጋት ሚናቸውን እንደሚጫወጡ ሊቀመንበሩ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የአሸባሪው ቡድን እስካልጠፋ ድረስ ኢትዮጵያ እንደ አገር ስላም እንደማትሆን የገለጹት ደግሞ የአማራ ሴቶች ማህበር ሊቀመንበር ወይዘሮ ትብለጥ መንገሻ ናቸው።

የክልሉ ሴቶች የአሸባሪውን ቡድን እኩይ ዓላማ ለማክሸፍ የትጥቅ ትግሉን እየተቀላቀሉ መሆናቸውን ተናግረውሴቶች ስንቅ በማዘጋጀትና ደም በመለገስ የሚያደርጉትን ተሳትፎ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አመላክተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.