የሀገር ውስጥ ዜና

ለህልውና ዘመቻው የምናደርገውን ድጋፍ አጠናክረን እንቀጥላለን – የምዕራብ ጎንደር ነዋሪዎች

By Meseret Awoke

October 21, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የህልውና ዘመቻው በድል እስኪጠናቀቅ ድረስ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የምዕራብ ጎንደር ዞን ነዋሪዎች አስታወቁ።

ለህልውና ዘመቻው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ከ10 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ሀብት ማሰባሰብ መቻሉ ተገልጿል።

ነዋሪዎች ”የሽብር ቡድኑ በሚንቀሳቀስበት አካባቢ መቆሚያና መቀመጫ መሬት በመከልከልና ባለበት በመደምሰስ ዳግመኛ ለበቀል እጁን እንዳያነሳ ማድረግ የግድ ነው” ብለዋል።

ወጣቶች ከታሪክ ተወቃሽነት ለመዳን ያላቸው ብቸኛው አማራጭ ከመንግስት ጎን በመሰለፍ የሽብር ቡድኑን መደምሰስ መሆኑን የገለጹት ነዋሪዎች ÷ ግንባር ድረስ ተሰልፈዉ ለመፋለም ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የዞኑ ሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ደረሰ አዱኛ ÷ የህልውና ዘመቻውን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ የዞኑ ህዝብ በአይነትና በገንዘብ እያደረገ ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለኢዜአ ተናግረዋል።

በተለይ ከዚህ ወር ጀምሮ የሰሊጥ ሽያጭ ወቅት በመሆኑ የተሻለ ሀብት ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን አብራርተዋል።

በድጋፉም የመንግስት ሰራተኞች፣ የንግዱ ማህበረሰብ፣ አርሶ አደሩ፣ ባለሀብቱና የተለያዩ ማህበራት ተሳትፈዋል ነዉ የተባለዉ።

የሽብር ቡድኑ ያለ የሌለ ሀይሉን በመጠቀም በንፁሃን ላይ እያደረሰ ያለውን ጭፍጨፋ ሁሉም ዜጋ በመነሳት መመከት እንደሚገባ አቶ ደረሰ አሳስበዋል።

በዞኑ ለህልውና ዘመቻው እስከሁን በተደረገ እንቅስቃሴ በአይነትና በገንዘብ ከ111 ሚሊየን ብር በላይ ማሰባሰብ እንደተቻለ ተመላክቷል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!